ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት አጠናከረች

Résumé détaillé
ኢትዮጵያ ከ2003 ጀምሮ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ድርድር እያካሄደች ሲሆን፣ አባልነቱ የወጪ ንግዷን ለማስፋፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚረዳ መንግሥት ይጠብቃል። ሆኖም ቀሪ የገበያ መዳረሻ ስምምነቶችና የሕግ…
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀውን የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ድርድር ለማጠናቀቅ አዲስ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ጥረት ጀምራለች።
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከኖቬምበር 9 እስከ 10 በተካሄደው ስምንተኛው የኢትዮጵያ አባልነት የሥራ ቡድን ስብሰባ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ያስሚን ወሃብረቢ ሰዒድ የአገሪቱን ልዑክ መርተዋል።
በልዑኩ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተሳትፈዋል።
የዓለም ንግድ ድርጅት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከ17 የሁለትዮሽ የገበያ መዳረሻ ድርድሮች 11ዱን አጠናቃ ስምምነት ፈርማለች። ቀሪዎቹን ስድስት ድርድሮች ለማጠናቀቅም እየሠራች ነው።
ሚኒስትር ያስሚን እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ፣ በጉምሩክ፣ በታክስ፣ በንግድ ፈቃድና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ያደረገቻቸው ማሻሻያዎች የአባልነት ሂደቱን ለማፋጠን የታለሙ ናቸው።
ኢትዮጵያ ከ2003 ጀምሮ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ድርድር እያካሄደች ሲሆን፣ አባልነቱ የወጪ ንግዷን ለማስፋፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚረዳ መንግሥት ይጠብቃል።
ሆኖም ቀሪ የገበያ መዳረሻ ስምምነቶችና የሕግ ማሻሻያ ጉዳዮች ገና መጠናቀቅ ስላለባቸው፣ ኢትዮጵያ የድርጅቱ ሙሉ አባል የምትሆንበት ቀን አልተወሰነም።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰቱ ያሉ የፖለቲካና የደኅንነት ችግሮችን በተመለከተ ከአውሮፓ ኅብረት የፖለቲካና የደኅንነት ኮሚቴ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዳለች።
በኖቬምበር 5 በአዲስ አበባ በተካሄደው ውይይት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራና የአውሮፓና የአሜሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር መለስ ዓለም ተሳትፈዋል።
Début de l'article, extrait de SBS News. Pour lire la suite, ouvrez l'article chez le média.
MarketNews présente le titre et le résumé publiés par le média. L'article complet se lit sur le site de l'éditeur. (www.sbs.com.au)